Call for Nomination for She Stands for Peace ebook - Amharic

16 Aug 2021

Call for Nomination for She Stands for Peace ebook - Amharic

የሴቶች፣ የሰላምና ደህንነት አጀንዳ በአፍሪካ ለማሳደግ ልዩ የሆኑ አፍሪካዊ ሴቶችን እዉቅና ለመስጠት “ለሰላም ትቆማለች” በሚል ርዕስ ለሚዘጋጀው የኤሌክትሮኒክ መፅሐፍ  የእጩዎች ጥቆማ ጥሪ

መግቢያ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለአፍሪካ ህብረት (UNOAU) እና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን (AUC) በጋራ በመሆን በየካቲት 2012  “ለሰላም ትቆማለች  በሚል ርዕስ የመታሰቢያ መጽሐፍ አሳትመዋል። 20 ዓመታት 20 ጉዞዎች 20ኛው ዓመት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ 1325 (2000)

በአህጉሩ የተመዘገቡ በርካታ ግጭቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሴቶች በሰላም ግንባታ ጥረት ውስጥ የሚጫወቱትን ጉልህ ሚና መጽሐፉ አጉልቶ አሳይቷል ይህ መጽሐፉ የአስራ ስድስት የአፍሪካ ሴት የሰላም መሪዎችን እና 4 ሴቶች የሚመሩ የሰላም ድርጅቶች የግለሰብ ታሪኮችን እና ልምዶችን ሰንዶ ይዟል። ህትመቱ የሴት የሰላም መሪዎችን እና ሴቶች የሚመሩ የሰላም ድርጅቶችን ጨምሮ በአህጉሪቱ ካሉ ሁሉም ንዑስ ክልሎች ብዙ ተነሳሽነትን ፈጥሯል።

የአፍሪካ ሴቶች ድምጽ ሴቶች በሠላም ግንባታ ጥረቶች ውስጥ የሚጫወቱትን ሚና ለማሳደግ እንደ መሣሪያ በመሆን የማይተካ ሚና አለው፡፡ በመሆኑም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለአፍሪካ ህብረት (UNOAU) በዚህ አውድ ውስጥ በመሆንለሰላም ትቆማለች” “She Stands for Peace” የሚል  የኤሌክትሮኒክ መፅሐፍ   eBook” እያዘጋጀ ይገኛል።   

የመጽሐፉ ዓላማዎች እና አንዳነድ ነገሮች

  • ሴቶችና በሴቶች የሚመሩ የሰላም ድርጅቶች በመላው አህጉሪቱ በሰላም ግንባታ ጥረቶች ያደረጉትን አስተዋፅኦ እውቅና መስጠት
  • በተለያዩ ደረጃዎች በሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ  የሴቶችን ዘላቂ ሰላም ከመገንባት አንጻር የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በማብራራት እና  የኑሮ ልምዶችን መመዝገብ  ማስቀመጥ፤
  • በአፍሪካ ውስጥ የሴቶች፣ ሰላምና ደህንነት  አጀንዳ ተግባራዊ ለማድረግ፣ ወደፊት የሚመለከቱ ስልቶችን ለማጋራት እና ቀጣይ ሥራዎችን ለማሳወቅ በሰላም ግንባታ ውስጥ በ ወቅታዊ ልምዶች ላይ በመመሥረት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ 1325፣ ድህረ 2020 ተግባራዊ ለማድረግ
  • የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ 1325 መሠረት ባለድርሻ አካላትን ማቀናጀት እና ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የሴቶችን ተሳትፎ በሰላም ግንባታ ጥረት መደገፍ።

ለእጩነት ብቁ ለመሆን የሚያስፈልጉ ነገሮች

  • ግለሰቦች ወይም በሴቶች የሚመሩ የሰላም እና ደህንነት ድርጅቶች ሊመረጡ ይችላሉ፡፡
  • ራስን እጩነት ማቅረብ ይበረታታ፡፡
  • በዕጩነት የሚቀረቡ ግለሰቦች ሴት  የአፍሪካ ሕብረት አባል አገሮች  ውስጥ ዜጋ መሆን አለባቸው።
  • እጩዎችን ለማቅረብ የዕድሜ ገደብ የለም መጽሐፉ በትውልዶች ውስጥ የወጣት እና ልምድ ያካበቱ መሪዎችን ስኬት ይመዘግባል።

ለእጩነት ብቁ ለመሆን  መስፈርቶች

በሚከተሉት ዘርፎች በማንኛውም የሰላም እና የደህንነት አስተዋፅኦዎች ተፅእኖ ፈጣሩ  እጩዎች በእጩነት ሊቀርቡ ይችላሉ።

  • በሰላም ሂደቶች ውስጥ እና/ወይም ከሰላም ጋር በተዛመደ ውሳኔ አሰጣጥ ውስጥ በንቃት ተሳትፈዋል ወይም  በእንደዚህ ያሉ ሂደቶች ውስጥ የሌሎች ሴቶችን ተሳትፎ መቻችተዋል፡፡
  • ጾታዊ እና ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ለመከላከል እና/ወይም ግጭትን መከላከል እና በቅድመ ግጭት ማስጠንቀቂያ  ውስጥ የሥርዓተ -ፆታ ግንዛቤን በመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡
  • የሴቶችን እና ልጃገረዶችን ደህንነት የአካል እና የአእምሮ ጤና ኢኮኖሚያዊ እና አጠቃላይ ደህንነት እና/ወይም የሴቶች እና ልጃገረዶች መብቶች እና የሕግ ጥበቃዎቻቸው በእጅጉ እንዲሻሻል  አስተዋፅኦ አበርክተዋል።
  • ሴቶች ጉዳት ለደረሰባቸው እርዳታ እና ማገገሚያ አገልግሎት ለሚሹ  በተጨማሪም እንደዚህ ዓይነት ጥረቶች ውስጥ የሥርዓተ ፆታ አመለካከቶችን እንዲካተቱ ጉልህ ሚና ተጫውተዋል
  •  ከሴቶች፣ ሰላም እና ደህንነት ጋር የተዛመዱ አጀንዳዎችን  በንቃት በማስተዋወቅ ሌሎች በንቃት አሳትፈዋል፡፡
  •  ለለውጥ ተነሳሽ በመሆን ቁርጠኝነት፣ በመሰጠት እና  ጠንካራ የለዉጥ ስሜት በማሳየት በምሳሌነት መምራት ፡፡
  • በማኅበረሰቡ በብሔራዊ በክልላዊ እና/ወይም በአህጉራዊ  ደረጃ ሰላምና ደህንነትን በማስፋፋት ሌላ ጉልህ ሚና ተጫውተዋል።

እጩዎችን ለማቅረብ ቀነ ገደብ

እጩዎችን የማቅረቢያ  ጥሪው እስከ ረቡዕ መስከረም 20 ቀን 2022 (23:59 GMT) ድረስ ክፍት ይሆናል። እንደሚጠበቀው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አመመልካቾ ምክንያት የምርጫው ሂደት ከተጠናቀቀ በኋላ ከተመረጡ እጩዎች ብቻ ጋር ግንኙነት ይደረጋል

የእጩዎች አቀራረብ

  • እጩዎችን ከማቅረቦ በፊት እባክዎን እጩ የማቅረቢያ መስፈርቶቹን በጥንቃቄ ያንብቡ።
  • እጩዎችን ለማቅረብ የተዘጋጀውን ቅጹ ከድህረ ገፃችን ላ በመጫን እና  ቅጽን በመሙላት  በኢሜል አድራሻችን መላክ አለቦት።
  • የእጩነት ምዘናውን ለማድረግ እጩዎች ትክክለኛ ሁሉን አቀፍ እና የተሟላ መረጃ መስጠ አለባቸው።
  • በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሚሰሩ አፍሪካ ሴቶችና ሴቶች የሚመሩ የሰላም ድርጅቶች  በእጩነት እንዲቀርቡ ይበረታታሉ።
  • በገጠር በስደተኝነት ከቀያቸው በመፈናቀል እንዲሁም በአካል ጉዳተኝነት የሚኖሩ አፍሪካ ሴቶች እና ሴቶች የሚመሩ የሰላም ድርጅቶች በእጩነት እንዲቀርቡ ይበረታታሉ።
  • የሁሉንም የአፍሪካ ክልሎች ፍትሃዊ ውክልና ለማረጋገጥ የጂኦግራፊያዊ ሚዛንን ግምት ውስጥ በማስገባት ዕጩዎች ይዳኛሉ።
  • ዕጩዎችን በአማርኛ፣ እንግሊዝኛ በአረብኛ በፖርቱጋልኛ እና በፈረንሳይኛ ማቅረብ ይችላሉ። 
  • ጩዎች በሚዘጋጀ የኤሌክትሮኒክ መፅሐፍ  ውስጥ የሚታተም የቅርብ ጊዜ ፎቶ መላክ አለባቸው በተጨማሪም ኢሜል እና ስልክ ቁጥርን ጨምሮ የግል መረጃ በማመልከቻ ቅጹ  ውስጥ መጠቀስ አለበት።

ለማመልከት ቅጹ ከድህረ ገፃችን ላይ በመጫን እና  ቅጽን ይሙሉ። ሁሉንም ቅጾች  :   unoau-genderunit@un.org በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መላክ አለባቸው።

የእጩዎች ጥቆማ ውድቅ ሊደረጉ የሚችሉባቸው ሁኔታዎች

በሚከተሉት ምክንያቶች እጩዎች ጥቆማ ውድቅ ሊደረጉ ይችላል፡፡

  • በተወሰኑ ሴቶች፣ ሰላምና ደህንነት  አስተዋፅኦዎች  ላይ የማያተኩሩ ይልቁንም የዕድሜ ልክ ስኬቶችን የሚዘረዝሩ ከሆነ
  • ዶሴዎች ያልተጠናቀቁ እና /ወይም ሁሉንም ደጋፊ ሰነድ/ዎች ያላካተቱ ወይም ያልተያያዙ ከሆነ
  • የየትኛውም የአፍሪካ ህብረት ሰራተኛ ወይም የክልል ኢኮኖሚ ማህበረሰቦች እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞች ከሆኑ።
  • ሞልተው ያስገቡት ጥቆማ ግልፅ ሴቶች፣ ሰላምና ደህንነት አስተዋፅኦዎች ያልተገለፀ ከሆነ።